District of Columbia Office of Human Rights

06/23/2023 | Press release | Distributed by Public on 06/23/2023 16:42

የዳይሬክተር ማስታወሻ- ሰኔ 2023 (Amharic)

የተከበራችሁ ኗሪዎች፣ ጎረቤቶችና ጓደኞች፡

እስከአሁን ድረስ በ 2023 በተደረጉ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ስብሰባዎች፤ በመላይቱ አገር የሚገኙ የፖለቲካ ሰዎች፣ የግብረ-ሶዶማውያንን (LGBQT) መብቶች የሚገፉ ከ490 የሚበልጡ ጽንሰ-ሃሳቦች ህግ ሆነው እንዲደነገጉ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ እነኚህ ጽንሰ-ሃሳቦች በቅድምያ ወጣግብረ-ሶዶማውያንን የሚመለከቱ ሲሆኑ፣ በስድስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው- የጤና ጥበቃ ጉዳይ (130 ጽንሰ-ሃሳቦች)ትምህርት ቤቶችንና ትምህርት በተመለከተ (228)፣ የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት (43)፣ ወደ ትክክለኛው አይዲኤስ (IDS) መግባትን በተመለከተ(16)፣ የስብዓዊ መብቶችን ህጎች በማዳከም በኩል (40)፣ የህዝብ መገልገያዎችን በተመለከተ(8)፡፡ሌላም የቀረበ ሰባተኛ ጽንሰ ሃሳብ አለ፡፡ይህም ከሌሎች ከቀረቡት ጽንሰ ሃሳቦች ጋር ፍጹም የማይገናኝና የማይስማማ፤ ግብረሶዶማውያንን ከምድረ ገጽ ማጥፋት በሚል የቀረበ ሃሳብ ነው፡፡ የአሜሪካ የህዝብ ነጻነት ማህበር ኤሲኤልዩ (American Civil Liberties Union (ACLU)፤ የግብረሶዶማውያን ማህበረሰብን የሚያጠቁ፣ ሪኮርድ የሰበሩ (record-breaking ) 278ጽንሰ ሃሳቦችን ከመዘገበ በኋላ፤ለግብረ ሶዶማውያን የሚጣበቁ ሰዎችን፣ ድርጅቶችንና ደጋፊዎችን ለመርዳትና አንዳች እርምጃ እንዲወሰዱ ለመገፋፋት ዲጂታል ዳሽ ቦርድ(digital dashboard) አቋቋመ፡፡

ዲስትሪክቱ፤ በ 2023የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ግብረ ሶዶማውያንን የሚጻረር ወይም የሚቃወም ህግ እንዳይወጣ ከሌሎች ሶስት ክፍለሃገሮች (ዊስኮንሲን፣ ኢለኖይ እና ዴላዌር) ጋር ተስማማ ፡፡ይህ ብዙም የሚገርም ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም ዲስትሪክቱ ከ1970ጀምሮ የግብረ ሶዶማውያን ሰብዓዊ መብቶችን በግንባር ቀደምትነት ሲጠብቅላቸው ቆይቷልና፡፡ ግንቦት (May)23ቀን 1972፣ የዲሲ የትምህርት ቤቶች ቦርድ፣ በአጠቃላይ የሁሉንም የትምህርት ቤቶች ሰራተኞችን የስራ መቀጠር መብትን የሚመለከትና በዛውም የመጀመርያው የግብረ ሶዶማውያንን መብት የሚጠብቅ ህግ አስተላለፈ፡፡ዲስትሪክቱ፤ በስራ አቀጣጠር፣ በስራ ውስጥና በጡረታ እንዲሁም በስራ ምደባ ማንኛውም አድልዎ እንዳይደረግ ህግ ሲያስተላልፍ፤ ለመጀመርያ ግዜ ለሁሉም መማህራን የስራ ዋስትና ሰጠ ማለት ነው፡፡ በዛው ዓመት መጨረሻ ላይም፤ ዲስትሪክቱ፤ ግለኛነትን የሚመለከተውን የአሜሪካን ህግንና የዲሲን የሰዶም ህግ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ በአዋቂዎች መካከል በስምምነት የተደረገ ግላዊ የሆነ ጾታዊ ግንኙነት፤ እንደ ወንጄል ተቆጥሮ ለክስ እንዳይቀርብ ከለከለ፡፡

የግብረ ሶዶማውያን ማህበረሰብን ለመጠበቅ የሚካሄደው ጥረት እስከአሁን ድረስ በመቀጠል ላይ ይገኛል፡፡በቅርቡም፤ የምክርቤት አባል ትሬዮን ዋይት (Trayon White (ዋርድ 8Ward 8)፤ የ 2022 በስቶርሚያ ዴንሰን ጃክሰን የደረሰውን ጉዳት በኤኮኖሚ ማካካስ የፍትሃዊነት ህግ (Stormiyah Denson-Jackson Economic Damages Equity Act of 2022)የሚባለውን አስተዋወቀ፡፡ ይህ ህግ፤ በዲስትሪክቱ በአንድ የአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ራሱን በገደለ የ12-ዓመት ልጅ ስም የተሰየመ ነው፡፡ ይህ ህግ ያንን በላያቸው ላይ የተፈጸምባቸውን ጉዳት ወይም እስከሞት የሚያደርስ ተገቢ ያልሆነ ግፍን በተመለከተ የሚከፈለው የገንዘብ ካሳ በዘር፣ በቆዳ ቀለም፣ በሃይማኖት፣ በትውልድ አገር፤ በጾታና በጾታ ማንነት መገለጫ እንዲወሰን የሚያደርገው ህግ እንዲቋረጥ ያለመ ነው፡፡ ይህ ህግ በህዳር (November)ወር 2022ላይ በ ዲሲ ከንቲባ ሙሬል ባውዘር (Muriel Bowser)ጸድቆ፣ በጥር (January)ወር 2023ወደ ላይኛው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ቀርቦ፤ ከየካቲት (February)23ቀን 2023ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል፡፡

በአሁኑ ዓመት የትልቅ ኩራት ዓላማ (The theme for Capital Pride)ለማህበራዊ ፍትህ የቆሙ ድርጅቶች እንዴት አብዮት ፈጥረው የግብረ ሶዶምያውያንን የነጻነት ህይወት ሊያሻሽሉ በመቻላቸው ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ አድልዎና ጭፍን ጥላቻ የሚያከትሙት ሁላችንም ተባብረን በሁሉም ዓይነት መልካቸው እንዲጠፉ ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ ፤

በእርሶ ራስዎ ወይም እርሶ በሚያውቁት ሰውላይ፤ በትምህርት ተቋሞች፣ በስራ ቦታዎች፣ ቤትን በተመለከተ፣ በህዝባዊ አገልግሎቶች ወይም በመንግስት ተቋሞች ውስጥ አድልዎና ጭፍን ጥላቻ ተፈጽሟል የምትሉ ከሆነ፤ ስለዚሁ ጉዳይ በበለጠ ለመረዳትና የትና እንዴት መክሰስ እንደምትችሉ ለማወቅ በኦንላይን ወደ ohr.dc.govይግቡና ይመልከቱ፣ ለህዝብ ክፍት በሆኑ ስብሰባዎች(Open Houses) ተካፈሉ ወይም ስለዚሁ ጉዳይ ወደሚሰማባቸው (Listening Labs)ይግቡ ወይም የሰብዓዊ መብቶች ጥናቶች ወይም ሰብዓዊ መብቶችዎን ይወቁ (Human Rights Liaison Know Your Rights trainings) በሚባሉት ስልጠናዎች ተካፈሉ፡፡ ስለነዚህ ጉዳዮች ወይም ስልጠናዎች መረጃ ከፈለጉ በዌብሳይታችን (website) ውስጥና ምን አዲስ ነገር አለ (What's New) እና መጪ ጉዳዮች (Upcoming)በሚሉ በየወሩ በሚወጣው መጽሄታችን ውስጥ የሚገኙትን ጽሁፎች ይመልከቱ፡፡

በአጋርነት